የደራሼ ልዩ ወረዳ የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ሆንዋል ተባለ

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ትናንት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ቁጥራቸው በውል ባልታወቁ ሰዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹ እንዳሉት ትናንት በልዩ ወረዳው ሀጠያ እና ሥለሌ በተባለ ቀበሌያት ከቀትር እስከ ምሽት በዘለቀው የተኩስ ልውውጥ ሰዎች ሞተዋል፣ የተደናገጡ ነዋሪዎችም ወደ ጫካ ሸሽተዋል፡፡…