መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል በኦሮሚያ ክልል ንጹሃንን እየገደለ ነው

መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል በኦሮሚያ ክልል ንጹሃንን እየገደለ ነው ሲል ኦነግ ትናንት ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ኦነግ ባለፈው ቅዳሜ ጭምር በምሥራቅ ሸዋ ዞን በድሮን ድብደባ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል።

በሰላማዊ ኦሮዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ ባስቸኳይ ይቁም ሲል የጠየቀው ኦነግ፣ መንግሥት ሠራዊቱን ከኦሮሚያ ክልል እንዲያስወጣ ጠይቋል።

ፓርቲው እየተፈጸመ ነው ላለው የንጹሃን ግድያ፣ የአማራ ክልል እና የሌሎች ክልሎችን ታጣቂዎች እና የኤርትራ መንግሥት ጭምር ተጠያቂ አድርጓል።