በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቃዮች የትንሳኤን በዓል እንዴት አከበሩ?

በግጭት እና ጦርነቶች ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እየጠየቁ፤ ከለት ወደ ዕለት የሚበረታው የኑሮ ውድነት ተጭኗቸው የትንሳኤ በዓልን አክብረዋል። ከ440 ሺሕ በላይ ዜጎች በመጠለያ በሚገኙበት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ትንሳኤ እንዴት ተከበረ? ሲል የዶይቼ ቬለው ነጋሳ ደሳለኝ ተፈናቃዮችን ጠይቋል።…