የብልፅግናው አደም ፋራህ ለኢዜማ መግለጫ መልስ ሰጥተዋል።

ለአምስት ዓመታት ሥልጣን በመረከብ ኢትዮጵያን አበለፅጋለሁ፣ ወደፊት አሻግራታለሁ፣ ያለው ብልፅግና ፓርቲ ራሱ ችግር ውስጥ መግባቱን፣ የኢትጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በመግለጫው ማሳወቁ ይታወሳል። ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ አካላት የእርስ በርስ እሰጥ አገባ ለአገር ሥጋት መፍጠሩንም ኢዜማ አሳውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ በግጭት ጠማቂነትና በኮንትሮባንድ አባወራነት ስማቸው በስፋት የሚነሳው የብልፅግና አዲሱ ተሿሚ አደም ፋራህ ለኢዜማ መግለጫ በፋና ቴሌቭዥን ቀርበው መልስ ሰጥተዋል።