አበርገሌ ውስጥ በተከሰተ የመድኃኒት እጥረት የሰዎች ሕይወት ሕይወት ማለፉ ተገለፀ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ ውስጥ በተፈጠረ የመድኃኒትና የምግብ አቅርቦት እጥረት ምክኒያት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱን የወረዳው አስተዳዳሪ ገለጹ፡፡

የህፃናትና የአዛውንት ሟቾች ቁጥር እንደሚበዛ ተናግረዋል። አብዛኞቹ ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነበረባቸው አስተዳዳሪው ገልፀው፤ የሞታቸው ምክኒያት ግን የመድኃኒት እጥረት መሆኑን ጠቁመዋ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአበርገሌ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሚገባ የብሔረሰብ አስተዳዳር ዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።