ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ለአስተዳደራዊ ስራዎች ማስፈጸሚያ ወደ ትግራይ ተልኳል – መንግስት

የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት ትግራይ ዉስጥ ለችግር ለተጋለጠዉ ሕዝብ ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ አበክሮ እየጣረ መሆኑን አስታወቀ። የፌዴራል መንግሥት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እንቅፋት ካልፈጠረ በስተቀር ረጂ ተቋማት «አስፈላጊ» ያሉትን የዕርዳታ ቁሳቁሶች በሙሉ እንዲያጓጉዙ መንግሥት ሙሉ ትብብር እያደረገ ነዉ።የዕርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት ለትግራይ ሕዝብ በየቀኑ 300 ተሸከርካሪዎች እሕል፣ በየሳምንቱ ደግሞ 200 ሺህ ሊትር ነዳጅ ያስፈልግዋል።

እንደ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍን የሚያደርጉ እና የሚያስተባብሩ 73 ድርጅቶች አሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ 17ቱ በየብስ የእርዳታ ቁሳቁስን ወደ ትግራይ ለማጓጓዝ ይረዳ የነበረው የሰመራ-አባዓላ-መቀለ ኮሪደር መዘጋትን ተከትሎ ከባለፈው ጥር ወር ወዲህ በአየር ትራንስፖርት አማራጭ

Äthiopien Mekelle | WFP Nahrungsmittellager ከ337 ሺህ ኪ.ግ.በላይ መድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች እና አልሚ ምግቦችን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ማጓጓዛቸውንም ኮሚሽኑ ይገልጻል፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ዓርብ እና ቅዳሜ በአባዓላ ኮሪደር በየብስ ትግራይ የደረሰው 500 ሜትሪክ ቶን የምግብ ቁሳቁስና 47 ሺህ ገደማ ሊትር ነዳጅ መንግስት ከረጂ ድርጅቶች ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የእርዳታ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዳይገባ እንቅፋት ይፈጥራል መባሉን ነቅፈው ያጣጣሉት አቶ ደበበ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ለሰብዓዊ እርዳታ እና ለአስተዳደራዊ ስራዎች ማስፈጸሚያ መላኩንም አውስተዋል፡፡ ከሃምሌ እስከ መጋቢት ወር ብቻም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ብቻ 57 በረራዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ በማድረግ ድጋፎችን ማመላለሱንም ነግረውናል፡፡
የዓለማቀፉ ምግብ ፕሮግራም (WFP) በበኩሉ ከባለፈው ታኅሣስ ወር ወዲህ የመጀመሪያው ነው ያለውን ከአጋሮቹ ጋር ባለፈው ቅዳሜ በየብስ መቀሌ ያደረሰውን 500  ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እና 47 ሺኅ ሊትር ነዳጅ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚጠባበቁ 5 ሚሊየን ህዝብ ለመድረስ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው ብሏል፡፡
Äthiopien | Binnenvertriebene aus Tigray ከዚህ ውስጥ በስድስት ተሽከርካሪዎች ከ200 ቶን በላይ የሚገመተውን የእርታ ቁሳቁስ በየብስ ያደረሰው የዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ነው፡፡ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ፋጥማ ሳተር ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት በትግራይ ባለው የህክምና ቁሳቁስ ችግር አንድ የእጅ ጓንት እንኳ የህክምና ባለሙያዎች በጋራ ለበርካታ ጊዜያት ለመጠቀም መገደዳቸው የአየር ትራንስፖርት በመጠቀም እርዳታውን ሲያደርሱት እንደነበር ያብራራሉ፡፡ አፕ… “እኛ እንደ ዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፈው ቅዳሜ ወደ ትግራይ በየብስ በዓባኣላ በኩል የላክነው የህክምና እና አስቸኳይ የምግብ ቁሳቁሶችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ በየብስ በ6 ወራት የመጀመሪያው መሆኑ ነው፡፡ በርግጥ በጥር ወር አካባቢ የየብስ መተላለፊያው መዘጋቱን ተከትሎ ከዚያን ወዲህ ብቻ በ40 በረራዎች የህክምና ቁሳቁሶችን ስናደርስ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የሰመራ-አባዓላው መንገድ ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ የግድ በሚያስፈልግበት ወቅት መከፈቱ መልካም ነው፡፡”

Symbolbild Äthiopien Ankunft des Konvois mit Hilfslieferungen in Tigrayዓለማቀፍ ረጂ ተቋማቱ በቀጣይ በትግራይ ያለውን ሰብዓዊ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በየቀኑ 300 እርዳታን የጫኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ መግባት መቻል አለባቸው እያሉ ነው፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በአንድ ተሸካርካሪ ትግራይ ከገባው 47 ሺህ ሊትር ነዳጅ አንጻርም እርዳታውን ለማቀላጠፍ 200 ሺህ ሊትር ነዳጅ በየሳምንቱ ወደ ክልሉ እንዲገባ መፈቀድ እንዳለበትም እየጠየቁ ነው፡፡ የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር የህ/ግንኙነት ኃላፊው አቶ ደበበ ዘውዴን ስዚህም ጠይቄናቸዋል፡፡ አፕ…
የዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቃል አቀባይዋ ፋጥማ ሳተር የሰብዓዊ ድጋፉ ትብብር ጅማሮውን መልካም ምልክት ያለው ብለውታል፡፡  “በቅርቡ የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ መተላለፉ በርካታ የሚያስፈልጉንን የእርዳታ ቁሳቁሶች በፍጥነት ለማዳረስ ስለሚረዳን በጥሩ ጎኑ የምንቀበለው ነው፡፡ የሚፈለገውን ሰዎችን የመርዳት ግባችንም እንደሚያሳካ እናምናለን፡፡”

የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቃል አቀባዩ አቶ ደበበ ዘውዴ ግን የተጀመረውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማጠናከር ሌላኛው ወገን ያሉትን የህወሓት ትብብርም ወሳኝነት እንዳለው አመልክተዋል፡፡ ከረዥም የውዝግብ ጊዜ በኋላ 20 ሰብአዊ ርዳታ የጫኑ መኪኖች ባሳለፍነው ዓርብና ቅዳሜ ትግራይ መቐለ ከደረሱ በኋላ በተጨማሪነት የተላከ የድጋፍ ቁሳቁስ አለመኖሩን የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማሳወቁን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል።