የአማራ ክልል የመልሶ ግንባታ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ

የአማራ ክልል የመልሶ ግንባታ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ

የአማራ ክልል ጦርነት በተካሄደባቸው ዘጠኝ ዞኖች የደረሰውን ውድመት ለመመለስ ይረዳል ያለውን፣ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ክልሉ ከዚህ ቀደም የደረሰውን ውድመት የሚያጠና ቡድን ጦርነት ወደ ተካሄደባቸው አካባቢዎች የላከ ሲሆን፣ አሁን እየተቀረፀ ያለው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የአጥኚ ቡድኑ ግኝቶችን መሠረት ያደረገ መሆኑን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡