የሰሞኑ የፈንታሌ ጥቃት የአማራና የኦሮምያ ዞኖች ባለሥልጣናትን እያነጋገረ ነው

በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ በተፈፀመ ጥቃት ሥምሪት ላይ የነበሩ የኦሮምያ የፀጥታ ጥበቃ አባላትና አንድ የአካባቢ ሚሊሽያ አዛዥን ጨምሮ 26 ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

ሌሎች 15 ሰዎች መቁሰላቸውን ለቪኦኤ የተናገሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ ለጥቃቱ ከአማራ ክልል የመጡ” ያሏቸውንና “የፋኖ ሚሊሽያ” እንደሆኑ የገለጿቸውን ታጣቂዎች በተጠያቂነት ከስሰዋል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ጎጥ ላይ እንደተፈፀመ የተገለፀው ይህ ጥቃት “ማንነታቸው ባልታወቀ አካላት የተቀነባበረ ነው” ሲል የዞኑ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መምሪያ ገልጿል።

“የኦሮምያ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በፋኖዎቹ ተገድለዋል” የሚለውን የኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መግለጫም እንደማይቀበሉት የመምሪያ ኃላፊው መሐመድ አህመድ ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ያዳምጡ።