የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተባለ።

አዲስ እየተዘጋጀ ያለው የሚዋጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል እርግዝናን በመከላከል ረገድ 99 በመቶ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ። የወሊድ መከላከያ እንክብሉ በአይጥ ላይ በተደረገ ሙከራ እርግዝናን ለመከላከል ውጤታማ መሆኑ እንደተረጋገጠ ስካይ ኒውስን ጠቅሶ አል ዓይን አስነብቧል።

በትናትናው እለት በአሜሪካ ኬሚካል ሶሳይቲ ስብሰባ ላይ ግኝታቸውን ያቀረቡት ተመራማሪዎች፤ አዲሱ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲሱን ግኝት ያቀረቡት ዶክተር በአብደላ አል-ኖማ፤ ተመራማሪዎች ለአስርት ዓመታት ያክል በአፍ የሚወጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ለመፍጠር ሲጥሩ ቆይተዋል፤ ሆኖም ግን እስካሁን እውቅና የተሰጠው መድሃኒት በገበያ ላይ የለም ብለዋል።

የወንዶች የወሲብ ሆርሞን ቴስቴስትሮንን ኢላማ ያደረጉ በርካታ ክሊኒካል ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን ያነሱት ዶክተር አብደላህ፤ ሆኖም ግን ከልክ ያለፈ የሰውነት ውፍረትን፣ ድብርትን እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ ናቸው ብለዋል።

አሁን የተሰራው የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ግን ከሆርሞን ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በቅርቡ በሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

ከሴቶች በተለየ ወንዶች እንደ ለወሊድ መከላከያነት ኮኖዶምን የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ከዚህ ከዘለለ “ቫሴክቶሚ” የተባለ እና በቋሚነት እንዳይወልዱ የሚያደርገውን የቀዶ ጥገና አማራጭ ብቻ ነው ያለው። በወንዶች ላይ ለወሊድ መከላከያ የሚደረገው “ቫሴክቶሚ” የተባለው ቀዶ ጥገና ህክምና በዋጋው ውድ ሲሆን፤ ብዙም ስኬታማ እንዳልሆነ ይነገራል።