ድርድሩን ተከትሎ የፌዴራል መንግስቱና ሕወሓት ተኩስ እናቆማለን ሲሉ በየፊናቸው መግለጫ በተመሳሳይ ሰዐት ለቀዋል።

ድርድሩን ተከትሎ የፌዴራል መንግስቱና ሕወሓት ተኩስ እናቆማለን ሲሉ በየፊናቸው መግለጫ በተመሳሳይ ሰዐት ለቀዋል። ሁለቱም በመግለጫቸው በሰብዐዊነት ላይ የተመረኮዘ የተኩስ አቁም አድርገናል ብለዋል። የአሜሪካ ልዑክ አዲስ አበባ መተው መመለሳቸውን ተከትሎ ወዲያው የወጣው መግለጫ ከናይሮቢ የድርድር መረጃዎች ጋር መገታተሙ የፖለቲካውን ጉዳዮች ሂደት አመላካች ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ተኩስ አቁም አወጀ

የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲል ከትግራዩ ሕወሃት ጋር የገባበትን ግጭት ለማቆም መወሰኑን የመንግሥት ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በርካታ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ፍለጋ ወደ አጎራባች ክልሎች እየተፈናቀሉ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ መንግሥት የክልሉ ነዋሪዎች ከክልላቸው ሳይወጡ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ ለማስቻል እና የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ሲል ከዛሬ ጀምሮ ግጭት ማቆሙን ገልጧል። የመንግሥት ውሳኔ ውጤታማ የሚሆነው ግን የትግራይ አማጺያን ተመሳሳይ ርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ ሲሆን እንደሆነ የጠቆመው መግለጫው፣ አማጺያኑ ከጥቃት እንቅስቃሴዎች እንዲታቀቡ እና በአጎራባች ክልሎች በኃይል ከያዟቸው አካባቢዎች እንዲወጡ ጠይቋል።

የትግራይ ክልል መንግሥት ተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ልክ እንደ ድሮው ዛሬም ጦርነት ምርጫችን አይደለም ያለው የክልሉ መንግሥት፣ በትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ልክ ዕርዳታ ስለመግባቱ ማረጋገጫ ከተገኘ ወዲያውኑ ተኩስ ለማቆም ዝግጁ ነን ብሏል።

መንግሥት ያልተገደበ ዕርዳታ ለትግራይ እንዲገባ ተጨባጭ ርምጃዎችን እንዲወስድም መግለጫው አሳስቧል። መንግሥት በተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔው ሕወሃት ከተቆጣጠራቸው የአጎራባች ክልሎች አካባቢዎች እንዲወጣ ላቀረበው ጥያቄ ግን፣ የክልሉ መንግሥት ምላሽ አልሰጠም።