የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ የሚገኙት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 በሚቆይ የስራ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት (AU) እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ባለስልጣናት እንዲሁም ከሰብአዊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነው።

ልዩ መልዕክተኛው ትላንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴኦዬ ጋር መክረዋል።

ምክክራቸው ትኩረቱን ያደረገው በሱዳን እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ጉዳዮች ላይ እንደነበር ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚታየውን አለመረጋጋት ለመፍታት የሾመቻቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከዚህ ቀደምም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበሩ አይዘነጋም።