ከመንግሥት ሹማምንት የሚፈለገው ሕግ ማክበር ብቻ ነው!

ከመንግሥት ሹማምንት የሚፈለገው ሕግ ማክበር ብቻ ነው!የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ጉባዔ ለተመረጡት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሰጡት ማብራሪያ፣ አባላቱ በአራት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ እነሱም ሕግ፣ ታሪክ፣ ህሊና፣ እንዲሁም ፈጣሪ ናቸው፡፡ የገዥው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በፌዴራልና በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በኃላፊነት ወንበር ላይ የሚቀመጡ በመሆናቸው፣ ደግሞ ደጋግሞ ሕግ እንዲያከብሩ ማሳሰብ ያስፈልጋል፡፡ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የሚቀመጥ ማንም ሰው (ሁለቱንም ፆታዎች ይወክላል) ከምንም ነገር በፊት ሰላማዊና ሕግ አክባሪ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ይኸው ሰው ለተሰጠው ኃላፊነት ግልጽነትና ተጠያቂነት ሊኖርበት ይገባል፡፡ ሥራውን ሲያከናውን ከብሔር፣ ከእምነት፣ ከፆታ፣ ከቋንቋ፣ ከባህል፣ ከፖለቲካ አቋምና ከመሳሰሉ መድሎዎች የፀዳ መሆኑን በተግባር ማሳየት ይኖርበታል፡፡ ለተሰጠው ኃላፊነት የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት፣ ብቃትና ሥነ ምግባርም መላበስ አለበት፡፡ በግሉ የሚከተለው ሃይማኖት፣ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም፣ የኑሮ ዝንባሌ ወይም የሕይወት ፍልስፍና ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ኃላፊነት ሲቀበል ደግሞ ግራና ቀኝ ከሚጎትቱት ስሜቶች ራሱን ነፃ ማውጣት ይጠበቅበታል፡፡ በዚህ ቁመና ላይ ሳይገኙ ሥልጣን ላይ መውጣት ተገቢ አይደለም፡፡

ተጨማሪ -> ከመንግሥት ሹማምንት የሚፈለገው ሕግ ማክበር ብቻ ነው! | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic