“በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የዲፕሎማቶች ቡድን ወደ ዩክሬን እያመራ ነው”

በጦርነት እየተናጠች ባለችው ዩክሬን በእስር ላይ የሚገኙ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ለማስለቀቅ በርሊን ከሚገኘው ኤምባሲ የዲፕሎማቶች ቡድን ወደ ዩክሬን እያመራ መሆኑ ተገለጸ። በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል የሚስዮን መሪ የሆኑት አምባሳደር ተፈሪ ታደሰ ለቢቢሲ እንደገለፁት ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ ከኤምባሲው የተውጣጡ የዲፕሎማቶች ቡድን ወደ ዩክሬን ለማምራት ረቡዕ ጠዋት ጉዞ ጀምሯል።…