የሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድር በቤላሩስ እየተካሄደ ነው

May be an image of 9 people, people standing and indoorየሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድር በዛሬው እለት በቤላሩስ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በቤላሩስ የሚደረገው የሁለቱ አገራት የሰላም ድርድር በዩክሬን የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻን ለማስቆም ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

ብዙ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎች ያሏቸውን የዶኔትስክ እና የሉጋንስክ ግዛቶችን ከጸረ-ሩሲያውያን ለመጠበቅ በሚል ሞስኮ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

ከወታደራዊ ዘመቻው ጥቂት ቀናት በኋላ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ÷ አገራቸው ከሩሲያጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የሚደረገው ድርድር በአገራቱ መካከል የተጀመረውን ጦርነት ማስቆም ያስችላል በሚል በተስፋ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይም አገራቱ የሰላም ድርድሩ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ቤላሩስ እያካሄዱ መሆኑን አርቲ ዘግቧል፡፡