የአፍሪካ ኅብረት በዩክሬን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀ-መንበር የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ማኪ ሳል እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት በዩክሬን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ ወገኖች በአፋጣኝ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደርሱ እና ያለ መዘግየት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኩል ፖለቲካዊ ድርድር እንዲጀምሩ ሳል እና ማኅማት አሳስበዋል።…