ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦነግ ጦር ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ተቀናጅቶ በነዳጅ ኮንትሮባንድ ላይ መሰማራቱን ደብቀዋል

” ነዳጁንም ቦቴውንም ውረሱት ብለናል ” – ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦነግ ጦር ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ተቀናጅቶ በነዳጅ ኮንትሮባንድ ላይ መሰማራቱን ደብቀዋል

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ” ነዳጅ ከኢትዮጵያ አውጥተው ወደ ጎረቤት ሃገር ወስደው የሚሸጡ ዘራፊዎች አሉ ” ብለዋል።

” ከራሳችን አልፍ ጎረቤት ሀገር ልንደጉም አንችልም ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” የሁሉም ክልል ሚሊሻዎች ልዩ ሃይሎች ፤ፖሊሶች ከሃገር የሚወጣ ነዳጅ ካገኛችሁ ነዳጁንም ቦቴውንም ውረሱ ብለናል ” ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ይበሉ እንጂ ባለፈው ሳምንት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኦነግ ጦር መንግስት ሸኔ የሚለው በነዳጅ ኮንትሮባንድ ላይ ተሰማርቶ ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ትብብር እየተደረገለት ወደ ጎረቤት አገሮች እየወሰደ በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። ይህንን ማስቆም ያልቻለ መንግስት የኦሮሚያ ባለስልጣናትና ልዩ ኃይሎች በነዳጅ ኮንትሮባንድ ተባባሪ በሆኑበት ወቅት ላይ ነዳጁንም ቦቴውንም ውረሱት ብለናል ማለት ቀልድ ነው።

ባለፈው ሳምንት ከተላለፉ የነዳጅ ኮንትሮባንድ ዘገባዎች ላይ አንዱን ከታች ይመልከቱት