ግልጽነት የጎደለው የሃገራዊ ምክክር መድረክ ኮሚሽን ፡ ከ632 እጩዎች ውስጥ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት እንደተመረጡ የሚያውቅ የለም።

በኮሚሽነርነት ለመሾም የቀረቡ ዕጩዎች ዝርዝር ከምስላዊ መረጃው ይመልከቱ።

የተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ 11 ግለሰቦችን ሹመት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ፈጣሪውም፣ አድራጊውም፣ ሿሚውም፣ አስረጅውም….. የብልጽግና ፓርቲ የሆነበት ግልጽነት የጎደለበት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት – ምንሊክ ሳልሳዊ

በጉጉት በሚጠበቀው ሀገራዊ ውይይት ሂደት ውስጥ ከሲቪል ማህበራት ስጋት ውስጥ አንዱ ኮሚሽነሮችን በመምረጥ ሂደት ላይ ግልፅ አለመሆን ነው። ከ632 እጩዎች ውስጥ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት እንደተመረጡ የሚያውቅ የለም። መንግስት በራሱ መራርጦ የፈለገው እንዲደረግለት የሄደበት አካሄድ ህዝብን ስላላሳተፈ በሃገር ላይ ለሚደርሰው አደጋ ብልጽግና ፓርቲ ተጠያቂ ነው። የዚህ ኮሚሽን እጣ ፈንታ እንደ እርቀ ሰላም ኮሚሽንና እንደ ወሰን ማካለል ኮሚሽን ይሆናል።

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ 11 ግለሰቦችን ሹመት የብልጽግና ፓርቲ የደረሰው ድርሰት ነው። ይህ ሹመት በርካታ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው። መንግስት ለተቃውሞው ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል። ፈጣሪውም አድራጊውም ሿሚውም አስረጅውም የብልጽግና ፓርቲ ነው ።

ተሿሚዎቹ የሁለት አገር ዜግነት ያላቸው፣ የሕወሓት አገልጋይና በኃላም የብልጽግና አምባሳደሮች የነበሩ፣ በርካታ ሃገራዊ ጉዳዮችን ያበላሹ፣ የህዝብ አመኔታ የሌለባቸውና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነታቸው የማይታወቅ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፖለቲካ ቅርብ የሆኑ የምሁር አደርባዮች ወዘተረፈ ናቸው። ይህ ግልጽነት የጎደለው ሹመት የኢትዮጵያን ሕዝብ ያገለለ የብልጽግና ፓርቲን አካሄድ የተከተለ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም። #MinilikSalsawi