በቤንሻንጉል ክልል ካማሼ ዞን በሚገኙ 5 ወረዳዎች የመንግስት ሥራ ከተቋረጠ ሁለት ወር እንዳለፈው ተገለፀ

መስከረም 15 2011 ዓ.ም ከቤንሻንጉል ጉምዝና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ አመራር አባላት በአሶሳ ላይ ስብሰባ አካሂደው ሲመለሱ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት 4 የካማሼ ዞን አመራሮች መገደላቸው ይታወሳል። ከዚህ ጊዜ በኋላ በዞኑ የመንግስት ስራዎች መቋረጣቸውንና ነዋሪዎችም ለችግር መጋለጣቸውን የክልሉ ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።…