ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ምርት አቋርጦ የነበረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ወደ ሥራ ተመለሰ

በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉ የስኳር ምርቱን አቋርጦ የነበረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ወደ ሥራ መመለሱን የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ ለቢቢሲ ገለጹ። ፋብሪካው ለሰባት ቀናት ያህል ከየካቲት 02፣ 2014 ዓ.ም ሥራ አቁሞ የነበረ ሲሆን የካቲት 8 ዳግም ወደ ሥራ መግባቱን ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረታ ደመቀ ተናግረዋል።…