በአዲስ አበባ የተከሰተው ነዳጅ እጥረት እያነጋገረ ነው ።

– በአዲስ አበባ በነዳጅ እጥረት ሳቢያ በተለይ ቤንዚን አለመኖሩ ጊዜያችንን በወረፋ እያጠፋን ስራችን እየተስተጓጎለ ነው። – የመኪና አሽከርካሪዎች
– የነዳጅ ሰልፉ ለእኛም ግልፅ አይደለም። እጥረት የተፈጠረው ለምን እንደሆነ ለማወቅም አልተቻለም። – የመንግስት ባለስልጣን
– ኦነግ ሸኔ በነዳጅ ንግድ ውስጥ እንዴት ሊገባ ቻለ? በነዳጅ ኮንትሮባንድ ውስጥ እነማን አሉ? – የኛ ቲቪ (ቪዲዮውን ከታች ይመልከቱት)

በአዲስ አበባ ከተማ ከሰሞኑ የሚታየው የነዳጅ ሰልፍ ምክንያቱ ምንድነው ?

በአዲስ አበባ የመኪና አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሳቢያ (ቤንዚን በተለይ) ረጅም ጊዜያቸውን በሰልፍ እያሳለፉ፣ የስራ ሰዓታቸውም እየተስተጓጎለ ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን እየገለፁ ይገኛሉ።

በበርካታ የነዳጅ ማደያ ቦታዎች ሰልፍ በመኖሩ ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት መቸገራቸው እና ረጅም ሰዓት ነዳጅ ለመቅዳት ተሰልፈው ለማሳለፍ እየተገደዱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከሰሞኑን በከተማው ውስጥ እየታየ ያለውን የነዳጅ እጥረት በተመለከተ ቃላቸውን ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት አቶ ታደሰ ኃይለማርያም (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ) ተከታዩን ብለዋል ፦

” የነዳጅ ሰልፉ ለእኛም ግልፅ አይደለም።

ብዙ ጊዜ ችግር የሚፈጥረው ቤንዚን ነው። የቤንዚን ጭነትን ብንመለከት ይሄ ነገር አዲስ አበባ ውስጥ በጣም ጎላ ብሎ የታየው ከጥር 23 ጀምሮ ነው።

ስለዚህ ከጥር 1 እስከ 23 ድረስ ባለው የተነሳው የነዳጅ መጠን ከጅቡቲ ኖርማል ነው። ታህሳስ ውስጥ የነበረው አማካይ እና ህዳር ውስጥ የነበረው አናካይ አሁን በዛን ወቅት ከተነሳው ምንም ልዩነት የለውም።

ለዚህ ነው በአቅርቦት ላይ ችግር የለም የምንለው፤ በመረጃ ተንተርሰን ከዛ በሚጫነው የጭነት መጠን መሰረት ነው።

… በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ ማለትም መርከብ ሊዘገይ ይችላል አንዳንድ እዛ በጭነት አካባቢ የሆነ ወጣ ገባ የሚል ነገር ካለ ያ አንድ ሶስት አራት ቀን ያን ፊክስ ለማድረግ የሚቆይ ስራ እና በስርጭቱ ላይ ችግር የሚፈጥር ከሆነ መንግስትን አስፈቅደን ከመጠባበቂያ እናወጣለን። ከዛ ያንን አውቶማቲካሊ ችግሩ ሲፈታ ተክተትን በዛ መልክ ነው የምንሰራው።

አሁን ይሄ እጥረት የተፈጠረው ለምን እንደሆነ ለማወቅም አልተቻለም።

… ሰልፎች አሉ ግን ያጠረ ነው። ከአራት እና ከአምስት ቀን በኃላ ወደ ኖርማል ሊመለስ ይችላል። ግን ትልቁ ችግር ለምን ይሄ ተፈጠረ ለሚለው መታየት አለበት። የዚህ ችግር ዋናው ምክንያት ምንድነው የሚለው ካልታየ ልክ በደረሰ ቁጥር ይሄ ነገር ጩኸት እየሆነ መቀጠል የለበትም። ማ ጋር ነው ? እኛ ጋር የቀርቦት ችግር ነበር የሚለውን ካለ መወቀስ እና እርምጃ መወሰድ አለበት፤ ሌላው አካል ጋርም ከሆነ በተመሳሳይ። ይሄ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ብቻ ችግሩን እያነሳን የምንሄድበት አካሄድ እኔ ጥሩ አይስመለኝም። ”

ኦነግ ሸኔ በነዳጅ ንግድ ውስጥ እንዴት ሊገባ ቻለ? | በነዳጅ ኮንትሮባንድ ውስጥ እነማን አሉ? ከታች ያለውን ቪዲዮ ያዳምጡት ።