የአፋር ህዝባዊ ኃይል ከመከላከል ወደ ማጥቃት በመሸጋገር ስትራቴጂክ ቦታዎችን ማስመለስ ችሏል።

ግጭቶችን ከፖለቲካዊ የኃይል አሰላለፍ አንፃር ብቻ የማየት አደገኛነት…  መሐመድ አ. ያሲን

May be an image of 1 person, standing and outdoorsበአሁኑ ወረራ የወያኔ ኃይል ከአፋር ወደ አምስት ወረዳዎች በቁጥጥሩ ስር ያዋለ ስሆን አሁንም በየቀኑ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ጦርነት እያካሄደ ይገኛል። በወረዳዎቹ ይኖሩ የነበሩ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅሏል። ከነዛ ውስጥ ግማሽ ያህሉ መንገድ በመዘጋቱ ለረሃብ ተጋልጦ ይገኛሉ። ይህ ሁላ ስሆን የፌዴራል መንግስት ባላየ አልፎታል። ሚድያው ሰለ ጦርነቱ ዘገባ እንዳይሰራ አፍነዋል። “ጦርነት የለም፣ በወረራ የተያዘ አካባቢም የለም” በማለት ክደዋል።

ወያኔ ልክ እንደ መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተደራጀ ኃይል አሰልፎ… ከጀነራል መድፍ እስከ ታንክ፣ ከዙ23 እስከ ሞርተር በአይነቱ የታጠቀ ኃየል ይዞ ነው ወደ አፋር የገባው። አፋር ግን በተቃራኒው በአብዘኛው ህዝባዊ ኃይል ሆኖ በዋናነት እንደ ክላሸና ብሬን አይነት ቀላል መሳሪያ የታጠቀ ኃይል ይዞ ነው ወደ መከላከል የገባው። እርግጥ ነው በመጀመሪያ ወረራም ተመሳሳይ ነገር ነበር የሆነው። ያሁኑ ለየት የሚለው ህዝቡ ያለ ከባድ መሳሪያ ድጋፍና ያለ ሰብኣዊ ድጋፍ ለብቻቸው ባልተዘጋጁበት ሁኔታ እንድዋጉ መደረጉ ነው።

“ጠላትን የመዋጋት፣ የተፈናቀለው ህዝብን የመደገፍ፣ ሰለ ወረራው ድምፅ የመሆን እዳ ሁሉ በእኛ ትካሻ ላይ ብቻ ወደቀ!”

ታዲያ እዚህ ጋር እንደ ሀገር ሊነሱ የሚገቡ ብዙ ጥያቄዎች ቢኖርም ቅሉ ጊዜው አይደለም በሚለው እንለፈውና። ሆኖም ግን እንደ አገር “ክልሎች በጣም ልያሳስባቸውና ልዘጋጁለት የሚገባ ትልቅ ትምህርት ያገኙበት ክስተት” ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለን እናምናለን። በተለይ ደግሞ አሁን ባለው የሴራ ፖለቲካ ውስጥ ጠላት በግልፅ ባልተለየበት የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ የሆነ አካል በድንገት ወረራ ልፈፀምብኝ ይችላል ብሎ ማሰብ ትክክል ይሆናል ማለት ነው። የፌዴራል መንግስትም ሆነ የቀሩ ክልሎች ወረራውን የሚለኩት ካለው የኃይል አሰላለፍና ለማዕከሉ ካለው ፋይዳ አንፃር እንጅ ከአገር ሉዓላዊነትና እንደ መንግስት ዜጎችን ከመጠበቅ ግዴታ አንፃር ባለመሆኑ ጉዳዩ አሳሳቢ ያደርገዋል።
እናም ድንበር ዘለል ግጭቶች የሚበራከትበትና ገና ያላለቁ የወሰን ጥያቄዎች በሞሉበት ቀጠና አሁን አፋር ላይ እየሆነ ያለው ሁኔታ የብዙዎች በር ማንኳኳቱ አይቀርም።

በመሆኑም ክልሎች አፋር ላይ አሁን ያለው ሁኔታ እንደ ማስጠንቀቂያ ደወል በመውሰድ በምላሹ “በነግ በኔ” መርህ ከአፋር ጎን መሰለፍ አልያም የራሳቸው የፀጥታ መዋቅር “ጠላት” በሚሉት ወገን ልክ መገንባትነና ሰነልቦናዊ ዝግጅት ማድረግ ግዴታ አድርጎ ልወስዱ ይችላሉ።

እዚህ ጋር በዋናነት የወረራ ሰለባ የሆነው ክልል ደግሞ ያሁኑ ወረራ የመመከት፣ በቀጣይ የሚመጡ መሰል ወረራዎችን ቀድሞ መከላከል የሚያስችል ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም መገንባት እንደ ህልውና ጉዳይ መውሰዱ አይቀርም።

በመሆኑም አፋር በመጀመሪያው ወረራ ላይ የማረከው ታንኮችንና መድፎችን ለመከላከያ አሳልፎ መስጠቱ አሁን ላይ እንደ ስህተት በማየት በቀጣይ መሰል ስህተት ላለመፈፀም ስራ መስራቱ ግዴታ ይሆናል። ወረራው ካገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከጎርቤት ሀገራትም ልመጣ ይችላል የሚለው ሌላኛው ስጋት ነው። ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያላባራው የአፋር/ሱማሌ ጦርነት ላይ የጅቡቲና የሱማሌ መንግስታት ሚና የሚታወስ ነው። አሁንም ክፍተት እየጠበቁ ነው። ኤርትራ ከወያኔ ጋር ለሚኖረው ጦርነት Buffer zone ለማገኘት አፋርን ልወር ይችላል… ወዘተ

በመሆኑም ክልሎች የፌዴራል መንግስት ከአሸባሪ ኃይልና ከማንኛውም ወረራ ይከላከለኛል የሚለውን መጠበቁ እንዳስበላው/እንደሚያስበላው/ በማመን የራሱን ኃይል ወደ ማደራጀት ልገባ ግድ ይላል። ከአፋር ጋር ተመሳሳይ ኬዝ ያላቸው እንደ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ አማራ ክልሎች ይህንን ሃሳብ የሚጋሩ ይመስለኛል።

******
ማሳረጊያ: ከትናነት ጀምሮ የአፋር ህዝባዊ ኃይል ከመከላከል ወደ ማጥቃት በመሸጋገር ስትራቴጂክ ቦታዎችን ማስመለስ ችሏል። በአጭር ግዜ ውስጥም ሙሉ በመሉ እንደምናስወጣቸው አንጠራጠርም። በዛውም አፋር ከእንደገና በዬተኛውም ኃይል እንዳይወረር በአላህና በራሱ አቅም ብቻ እንድመካ የሚያስችል ስራ ይሰራል ብለን እናምናለን። መሐመድ አ. ያሲን