ሳፋሪኮም – ኢትዮጵያ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሥራ እንደሚጀመር ተነገረ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቁጥጥርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ለካፒታል እንደነገሩት ከመንግስት ጋር ያላቸው ስምምነት እንደሚያሳየው የፍቃድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠኝ ወር ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርባቸው ገልፀው ከመጪው ሚያዝያ 9,2021 /እ.ኢ.አ/ጀምሮ በይፋ የንግድ ሥራ ለመጀመር እየሰራን ነው በለዋል ።
ከሐምሌ 9 2021 ጀምሮ የሚቆጠር የመሥሪያ ፍቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የቴሌኮም ማስፋፊያ ስራዎችን ጀምሯል። ባለፈው ወር የኩባንያው የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከል ስራ የጀመረ ሲሆን ኩባንያው የኔትወርክ ዝርጋታውን እየሰራ ነው።
ሁለት የኔትወርክ አቅራቢዎች ማለትም ኖኪያ እና ሂዋዌ ጋር እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው በአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለውን የኮር ኔትወርክ መሠረተ ልማት ኖኪያ ኩባንያ የሚሠራ ሲሆን ሁዋዌ ቀሪውን የአገሪቱን ክፍል ይሸፍናል ብለዋል
የመሰረተ ልማት መጋራት በተመለከተም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እስካሁን ስምምነቱ የለንም ነገር ግን በድርድር ደረጃ ላይ ነን ብሏል። ከመሰረተ ልማት ጎን ለጎን የሳፋሪ ኮም ደንበኞች እና የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች እንዲገናኙ ለማድረግ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጿል ።

ምንጭ ካፒታል ጋዜጣ