አሜሪካ በአፋር ክልል አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ እንዳሳሰባት ገለጸች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በአፋርና በትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ አሳስቦኛል አለ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ጥር 18/2014 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው” ብለዋል።…