ኢትዮጵያ ካመጠቀቻቸው ሳተላይቶች የሚገኙ መረጃዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ አይደለም ተባለ
–
ኢትዮጵያ ታኅሣሥ 10/2012 ያመጠቀቻት የመጀመሪያዋ ‹‹ETRSS1›› ሳተላይት እና ያንን ተከትሎ ከዓመት በኋላ የመጠቀችው ኹለተኛዋ ‹‹ET-Smart-RSS›› ሳተላይት የሚልኩትን መረጃ ወስዶ፣ አገራዊ ጥቅም ላይ የሚያውል ተቋም አለመኖሩን አዲስ ማለዳ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጣለች።
–
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው፣ መረጃዎችን ከሳተላይቶች ተቀብሎ እና ተንትኖ መረጃ ቢያመርትም፣ መረጃዎች ለተፈለገው ዓላማ የሚጠቀም ተቋም የለም።