የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ እስከ መጪዉ ታሕሳስ አጋማሽ ድረስ ሥራዉን እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ እስከ መጪዉ ታሕሳስ አጋማሽ ድረስ ሥራዉን እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ።የኮሚቴዉ መሪዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ኮሚቴዉ ያዋቀራቸዉ አራት ንዑሳን ኮሚቴዎች፤ ጥናት እና ሥራቸዉን ከሞላ ጎደል አጠናቅቀዋል።በየንዑሳን ኮሚቴዎቹ የተደረጉ ጥናቶች እና ሥራዎች ላይ ዉይይቶች ተደርጎባቸዉ አዳዲስ ሐሳቦች ተካትቶባቸዋል።በመግለጫዉ መሠረት በጥናቶች፤ በተሰበሰቡ አስተያቶች እና በተከናዎኑ ተግባራት ላይ በተመረጡ ከተሞች ተጨማሪ ዉይይት ተደርጎ የመጨረሻዉ ዉጤት ትሕሳስ 15 ይጠናቀቃል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE