ፍርድ ቤት አቶ አብዲ ኢሌ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

ፍርድ ቤቱ የሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ዑመር ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው።

ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ላይ የ10 ቀን ምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት መርማሪ ፖሊስ ከሃምሌ 26 ቀን እስከ 30 ቀን 2010 ዓ/ም በሶማሌ ክልልና በአካባቢው በተፈጸመው ወንጀል ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን ምስክሮች ቃል መቀበሉን፣ 30 ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና ማስረጃ ማሰባሰቡን፣ የ62 ሰዎች የጉዳት መጠንን ማስረጃ በአማርኛ ማስተርጎሙን ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE