ጠ/ሚ ዐቢይ በአማራ ክልል ከሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጎንደር ውይይት እያደረጉ ነው

 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአማራ ክልል ጉብኝት ጀመሩ።

በቆዮታቸው በጎንደር ከተማ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን ያካሂዳሉ።

በተጀመሩ ፕሮጀክቶችም ጉብኝት አድርገዉ ወደ ሌላ ከተሞች ያመራሉ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአማራ ክልል ከሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጎንደር ከተማ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

ውይይቱም በክልሉ በሰዎች መሃል ግጭት በፈጠሩ ጉዳዮች ላይ የሀገር ሽማግሌዎች ችግሮቹን ለመፍታት እያደረጉት ባለው ጥረት ላይ ያተኮረ ነው።

የሀገር ሽማግሌዎቹ ከዛሬ በፊትም ተገናኝተው ሲወያዩ ቆይተዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አበይ ጎንደር ከተማ ሲደርሱም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አደርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጎንደር የገቡት በነገው እለት በአማራ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር የሚገቡትን የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመቀበል ነው።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከነገ ጀምሮ በጎንደር እና ባህር ዳር ከተሞች ጉብኝት ያደርጋሉ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በነገው እለት ጎንደር ከተማ የሚገቡ ሲሆን፥ በቆይታቸውም በጎንደር እና አካባቢው የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሃገር ደረጃ የተጀመረውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።

በጎንደር ከተማ በርካታ ኤርትራውያን በተለያየ ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተመራ የልዑካን ቡድን በአስመራ ጉብኝት ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፡- ጠ/ሚ ጽ/ቤት

 

 

Image may contain: 7 people, people sitting

 

Image may contain: one or more people, people sitting and indoor

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE