አንድ ነን ብዙዎች፤ አንዶችም ብዙ ነን

የተፈጥሮ ሳይንስ ሊቃውንት ‹ዓለም በብዙ መልኩ የምትገለጥ ዉሑድ ዓለም ናት› ይላሉ፡፡ የተለያዩ የዓለም ከዊኖች ልዩ ልዩ ይምሰሉ እንጂ የአንዱ ዓለም ክፍሎች ናቸው፡፡ ከአንዱ ዓለም ጋር ተዋሕደውም የሚኖሩ ናቸው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ለብቻው ህልው ሆኖ ለመኖር የሚቻለው ማንም የለም፡፡ ሁሉም ፍጡራን ባለማቋረጥ እርስ በርሳቸው የሚገናኙ የተሣሠሩና የሚገነዛዘቡ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በየራሳቸው ከዊና…