የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና በአሜሪካ የሚያቀርቡ ድርጅቶች የ“ጉድ ፉድ አዋርድስ” ለተሰኘ ሽልማት እጩ ሆኑ

በአሜሪካ በተለይ የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና የሚያቀርቡ ድርጅቶች ለሽልማት ዕጩ ሆኑ በአሜሪካ በተለይ የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና የሚያቀርቡ 25 ድርጅቶች የ“ጉድ ፉድ አዋርድስ” ለተሰኘ ሽልማት እኤአ የ2019 ዕጩ መሆን ችለዋል፡፡በየአመቱ የሚካሄደው የሽልማት ፕሮግራሙ 2019 ለዘጠነኛው ዙር ሽልማት እጩ የሆኑ ድርጅቶችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ውድድር ከአሜሪካ ምድር ውጭ ከሚበቅሉ የምግብ አዝዕርት ለውድድር መሳተፍ የሚችለው ቡና ብቻ መሆኑም ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ ቡና በዚህ ውድድር ላይ ለዕጩነት ሲቀርብም ሆነ ሲሸለም የመጀመሪያው አይደለም፤ በ2018 በተደረገው የ“ጉድ ፉድ አዋርድስ” በቡና አምራችነት እጩ ሆነው ከቀረቡት 27 ድርጅቶች 26ቱ የኢትዮጵያን ቡና የሚያቀርቡ ሲሆን በዘርፉ 15ቱንም ሽልማት የወሰዱትም ከኢትዮጵያ ቡና እየቆሉ የሚያቀርቡት ድርጅቶች ናቸው፡፡

በ2019ኙ ውድድር ለመጨረሻው ዙር ከቀረቡት 25 ተሳታፊዎች ውስጥ 20ዎቹ ከኢትዮጵያ የመነጩ አልያም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቀላቅለው የሚያቀርቡ ድርጅቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ቀሪዎቹ 5ቱ ተወዳዳሪዎች ከኮስታሪካ፣ ከኮሎምቢያ ከጓቲማላ፣ ከፓናማ እና ከኬኒያ መሆናቸው ተውቋል፡፡

ምንጭ፡- ደይሊ ኮፊ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE