‹‹የአማራ የማንነት ጥያቄ አንስታችኋል›› ተብለው ከቀዬአቸው ተባረው አዲስ አበባ ከተማ የመጡ ተፈናቃዮች በፖሊስ መታገታቸው ተገልጾ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ቀረበ፡፡

መኖሪያቸውና የትውልድ ቦታቸው ወልቃይት ጠገዴ ተብሎ በሚታወቀው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሑመራና ቃፍታ ወረዳዎች የሆኑ 180 ግለሰቦች፣ ‹‹የአማራ የማንነት ጥያቄ አንስታችኋል›› ተብለው ከቀዬአቸው ተባረው አዲስ አበባ ከተማ የመጡ ቢሆንም፣ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ በፖሊስ መታገታቸው ተገልጾ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ቀረበ፡፡