ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያዩ

በውይይቱ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ፤ በተለይም በሴቶችን በቁልፍ የመንግስት አመራር ቦታዎች መሳተፍ መንግስታቸው እንደሚያደንቅና በሙሉ ልብ ለመደገፍና ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን ገልፀውላቸዋል፥፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ አገሪቱ በአህጉራዊ መድረክ እየተጫወተች ያለውን ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ያላቸውን ፍላጎት በስልክ ውይይታቸው ወቅት ጠቅሰዋል፥፥


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE