የባድመ ችግር ፈጠራ ነው – ምንም ዓይነት የድንበር ችግር አልነበረም (ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ)

የአልጀርስ የድንበር ውሳኔ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቶ የነበረው በውጭ ኃይሎች ጫና እንደነበር የገለፁት ፕሬዝዳንት ኢስይያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ አሁን በተፈጠረው ለውጥ፣ በኤርትራ ህዝብ ትግልና ፅናት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ብለዋል። “የባድመ ችግር ፈጠራ ነው። በሁሉም ሁኔታ ቢታይ ምንም ዓይነት የድንበር ችግር አልነበረም። የድንበር ችግር ቢኖርም በተለያየ መንገድመፍታት ይቻል ነበር” ያሉት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ  “ውሳኔው ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው በወያነ ስርዓት ሳይሆን፡ በዚያን ጊዜ በነበሩ የዋሽንግተን አስተዳደሮች እንጂ” ሲሉ ተናግረዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE