ጀነራል አብረሃ ወ/ማርያም ( ኳርተር ) 2ቢሊዬን ብር በልጆቹ ስም ማስተላለፉን የሚገልፅ ማረጋገጫ ተገኘ

ብሌን አብረሃ

ጀነራል አብረሃ ወ/ማርያም ( ኳርተር ) 2ቢሊዬን ብር በልጆቹ ስም ማስተላለፉን የሚገልፅ ማረጋገጫ ተገኘ

ጀነራል አብረሃ ወልደማርያም ( ኳርተር ) የምስራቅ ዕዝ አዛዥ በነበረበት ጊዜ በልጆቹ ስም ከሶማሌ ክልል ትራንስፖርትና ንግድ ቢሮ በባንክ ያስተላለፈበት የባንክ ሰነድ የቀኝ እጁ በሆነው ወልዴ አባገብረስላሴ በተባለው መኖሪያ ቤት ተገኘ። ጀነራሉ በልጃቸው ስም ያስተላለፉት የገንዘብ መጠን በብሌን አብረሃ ስም 47 ሚሊዮን ብርና በኖቤል አብረሃ ስም ደግሞ 1ቢሊዬን 953 ሚሊዮን ብር ያስተላለፈ ሲሆን ጀነራል አብረሃ በድምሩ 2ቢሊዬን ብር በልጆቹ ስም ማስተላለፉን የሚገልፅ ማረጋገጫ ተገኝቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የጀነራል አብረሃ ቀኝ እጅ የሆነው ወልዴ ለቀን ስራ ከደቡብ ክልል ወደ ጅግጅጋ ለመጡ የቀን ሰራተኞች 400,000 ብር በመክፈል ጅግጅጋን እንዲያተራምሩና እንዲሁም በሌላ ክልል ተወላጆች ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑንም በሰነድ ተረጋግጧል።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE