ሰሜን ወሎ ግጭት ለማረጋጋት በሞከሩ ሰዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ

በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ ግጭት ለማረጋጋት በሞከሩ ሰዎች ላይ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።በላሊበላ ከተማ ቀበሌ 01 ዛሬ ጠዋት በሁለት ሰዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ጉዳዩን ለማረጋጋት በሞከሩ ሰዎች ላይ ግለሰቡ ጥይት መተከሱን ፓሊስ አስታውቋል።

በዚህም የስምንት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ነው የተነገረው።የቆሰሉት ሰዎች አሁን ሆስፒታል ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ አስተባበሪ ምክትል ኮማንደር መሠረት ላቀ አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ኮማንደሩ እንደገለጹልን ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው፡፡

ምንጭ፥ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE