የአማራ ክልል ምክር ቤት በጫት አጠቃቀም ላይ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በከፊል አጸደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት በጫት አጠቃቀም ላይ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በከፊል አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 11ኛው መደበኛ ጉባዔው ጫት በዋና ዋና መንገዶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም በሆቴሎች እንዳይቃም በሚል በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ደግፏል፡፡

ቢሆንም ግን የቀረቡት ስምንት የውሳኔ ሀሳቦች በሙሉ ወዲያው ተግባራዊ ማድረግ እንደማይቻል ተናግሯል። ጫት ለሚሸጡ፣ ለሚያዘዋውሩና ለሚያከፋፍሉ ወጣቶችም መንግስት ሌላ የስራ መስክ እንዲያመቻችላቸው ጠይቋል፡፡ሂደቱን በአንዴ ማስቆም አስቸጋሪ በመሆኑ ጫት አደገኛነቱ በምክር ቤት አባላት በአቋም ተይዞ በሂደት የውሳኔ ሀሳቦች ተግባራዊ እንደሚሆን ምክር ቤቱ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል፡፡

አንዳንድ የምክር ቤት አባላት የውሳኔ ሀሳቡ በአስገዳጅ አዋጅ ሊደገፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ጫት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ በጉባኤው ተገልፃል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE