የኮንሶ ፤ የሀላባ እና የጎፋ ሕዝቦች በዞን የሲዳማ ሕዝብ በክልል ደረጃ ተዋቀሩ

ሕዝብ የሚያነሳቸዉ የራስ አስተዳደር ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በደቡብ መስተዳድር በተለያዩ አካባቢዎች አስከትለዋል።የደቡብ መስተዳድር ምክር ቤት በመስተዳድሩ የሚኖሩ የተለያዩ ብሔረሰብ አባላት በየጊዜዉ ላነሱት የራስ አስተዳደር ጥያቄ መልስ ይሰጣል ያለዉን የውሳኔ ሀሳብ ዛሬ አጸደቀ፡፡ሀዋሳ የተሰየመዉ የምክር ቤቱ ጉባኤ ባፀደቀዉ ዉሳኔ መሠረት የኮንሶ ፤ የሀላባ እና የጎፋ ሕዝቦች የሚኖሩባቸዉ አካባቢዎች በዞን አስተዳደራዊ መዋቅሮች ይደራጃሉ።ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም የሲዳማ ሕዝብን በክልል ደረጃ ለማዋቀር በቀረበው ጥያቄ ላይም በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE