ከምን ልታዘዝ ካፌ መሪ ተዋናዩ አያልቅበት (ሚካኤል ታምሬ) እና የትዕይንቱ ጸሃፊና ዳይሬክተር በኃይሉ ዋሴ ይናገራሉ

“ምን ልታዘዝ!”  የተከታታዮቹን ቀልብ ለመሳብ እና ተወዳጅነት ለማትረፍ ጭምር የታደለ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ነው – ከምን ልታዘዝ ካፌ መሪ ተዋናዩ አያልቅበት ሚካኤል ታምሬ እና የትዕይንቱ ጸሃፊና ዳይሬክተር በኃይሉ ዋሴ ይናገራሉ

“ሳታየር” (ስላቅ) ከተሰኘው የጥበብ ዘርፍ የሚመደብ፣ ፈጥኖም የብዙዎች የተከታታዮቹን ቀልብ ለመሳብ እና ተወዳጅነት ለማትረፍ ጭምር የታደለ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ነው – “ምን ልታዘዝ!”

በቀልዳ ቀልድ ለዛ የተዋበው ፖለቲካዊ ሥላቅ፣ በሥነ ጽሁፍ፥ በመድረክ አለያም በሥዕላዊ ሥራዎች አማካኝነት በማኅበረሠብ ውስጥ እየታዩ ያሉ ማኅበራዊ ህጸጾችንና ክስረቶችን ለመንቀስና ለመተቸት የሚሳል የጥበብ ዘዬ ነው። ፈታ-ዘና ብለው እንዲከተሉት የሚፈቅደው ይህ የጥበብ ዘዬ ታዲያ በአጫጭር ትዕይንቶች ይሞላ እንጅ ከኮርኳሪነቱ ጋር ቀልጠፍ ያለው ቅብብል ጭብጡን በቅጡ ከታዳሚው ከማድረስ አያገደውም።

ዘዬው በግለሰቦች የተፈጸሙ ድርጊቶችን ብቻ ሳይሆን በቡድኖች፣ አለያም በተቋማት፣ በአስተዳደርና በመንግስት ሲደረጉ የሚስተዋሉ ነገር ግን “ያልሆኑ” ጉዳዮች ይተቻል። ያጣጥላል።