በጅግጅጋ ከተማ ላይ ሁለት ሰዎች በፖሊሶች ሲገደሉ ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

RAJO = በጅግጅጋ ከተማ ላይ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ሁለቱ ሟቾች የሚከተሉት ናቸው

1. ሼክ አህመድ አብዱል በፌዴራል ፖሊሶች ከመስጊድ ሲወጣ የተገደለ
2. አቶ ወንድወሰን ደስታ በልዩ ፖሊስ ኃይሎች ከሥራ ወደቤቱ ሲያመራ የተገደለ

ወደ ቤተ-መንግስቱ አካባቢ የእርሻ መሬታቸው በልዩ ፖሊሶች በጉልበት የተነጠቀባቸውን ሰዎች ለመበተን ልዩ ፖሊሶች ባደረጉት ተኩስና ድብደባ ብዙ ሴቶችና አዛውንቶች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል ሌሎች ደግሞ ወደ ህክምና ሳይወሰዱ ልዩ ፖሊሶች አስሯቸዋል፡፡ ከትምህርት ቤት የሚወጡ 4 ተማሪዎችም ቆስለዋል

በአሁኗ ሰዓት ሶማሊ ያልሆኑ ወገኖቻችን በጅግጅጋ ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛል፡፡ ከሚያነሷቸው መፍክሮች ጎልቶ የሚሰማው “ሞት ይብቃ” የሚለው ነው፡፡

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE