ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ3 የአውሮፓ ከተሞች ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በ3 ቀናት ያካሄዱትን የ3 የአውሮፓ ከተሞች ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

በፓሪስ፣ በርሊን እና ፍራንክፈርት በእርሳቸው ለሚመራው ልዑክ ለተደረገው አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለዳያስፖራ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ በአውሮፓ ለሚገኙ የኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና ለሐገራቱ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የትዊተር መልእክት ለመረዳት ችለናል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE