ላሊበላን ለአደጋ በማጋለጥ ለመበልጸግ የቋመጡ የቅርስ ጥበቃ መስሪያቤት ሃላፊወችና ተባባሪወቻቸው በሕግ ሊጠየቁ ይገባል

(ሚኪ አምሃራ)

በላሊበላ ላይ ስለሚፈጸሙት ሁለት ሌብነቶችና መወሰድ ስላለበት እርምጃ በዚህ ዓጭር ገለጻ ላይ የቅርስ ጥበቃን ጥፋት በተመለከተ ስንናገር የቅርስ ጥበቃ ዓመራርን እና በተለይ ሃላፊውን እንጅ ሁሉም የቅርስ ጥበቃ ሰራተኞች ጥፋተኛ ናቸው እያልን ዓለመሆኑ በቅድሚያ ይታወቅልን።

ፍሬ ነገር:- ላሊበላን ለአደጋ በማጋለጥ ለመበልጸግ የቋመጡ የቅርስ ጥበቃ መስሪያቤት ሃላፊወችና ተባባሪወቻቸው ላሊበላ ላይ በፈጠሩት ዓደጋ በህግ መጠየቅ ሲኖርባቸው ዓሁንም ላሊበላን የማዳን ስራው መሪ መሆናቸው ዓስገራሚ ንቀት ነው። ላሊበላን ለማዳን የሚደረገውን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ መደረግ ካለባቸው ሞያዊ ተግባራት በተጨማሪ በህንጻው ላይ ዓደጋ ያመጣውን ብልሹና ህሊና ቢስ የቅርስ ጥበቃ መዋቅር ስርዓት ማስያዝ መዋል ማደር የሌለበት ተግባር ነው። ይህ ተግባር ላሊበላን የማዳን ጩኸታችንን ያሰምርልናል እንጅ ዓይጎትተውም። ቅርስ ጥበቃ ላሊበላ ላይ ያሰራው ይህ መጠለያ ወንጀል ነው- እርዳታ ዓይደለም። ወንጀል የሰራ ደሞ በህግ ይጠየቃል እንጅ ወንጀል የሰራበት ቅርስ ጠባቂ ተደርጎ አይሾምም።” ይህ የህዝባችን እና ለህዝባችን የሚቆረቆሩ ባለሞያወች ድምጽ ነው። ህዝባችን “ለመሆኑ ባገሪቱ ውስጥ የተማረ የለም ወይ? በማን አለብኝነት እኛን እያስፈራሩ ህንጻውን ሊያፈርስ የሚችል ብረት ሲተክሉ ለምን ብሎ የሚጠይቅ እንዴት ይጥፋ? ካህናቱ ደብዳቤ ያልጻፍልነት የመንግስት ባለስልጣን ወይም ዓለማቀፍ ድርጅት የለም። ለምን ተናቅን? ቅርሳችንን ለሞት አሳልፎ የሰጠው አካል ይጠየቅልን” እያለ ነው።

ህዝባችን “ተጠያቂነት ከሌለ ዓሁንም ገንዘብ ዓሰባስበው መጥተው ህንጻችንን ሊያስፈርሱት ይችላሉ። ሁልጊዜም ቢሆን ገንዘቡ ላይ እንጅ ስራው ላይ ትኩረት ዓይሰጡም” እያለ ነው። ህዝባችንም በሰላማዊ ሰልፍ የቅርስ ጥበቃን ወንጀል ገልጻል። በባለሞያወች ጥናት እያካሄድን ቆይተን ዛሬ ለዚህ ወሳኝ እርምጃ ደርሰናል።

መንደርደሪያ
ደርግ እንደወደቀ ያውሮፓ መንግስት ስልጣን ከያዘው ኢህአዴግ ጋር ለመቀራረብ ከዘረጋቸው መጠነ ብዙ ማታለያ እርዳታወች አንዱ ከአውሮፓ ህብረት የተገኘው 9.1 ሚሊዮን ዩሮ ነበር። ብሩ እንደተገኘ የመጠለያ ስራው ከመጀመሩ በፊት ግን ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የሚባል መስሪያ ቤት በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ ‘በነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 209/1992 ተቋቋመ። መስሪያ ቤቱ የሚገርም ሰፊ ስልጣን ተሰጠው። በማስታዋቂያና ባህል ሚኒስትር ስር ሆኖ ግን የቅርስ ሃብትን በተመለከተ ዓድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ተቋቋመ። የላሊበላ ህንጻ እድሳትም በቅርስ ጠበቃ ባለስልጣን እጅ ውስጥ ወደቀ:: እንግዲህ እዚህ ላይ ነው ከትውልድ ትውልድ ሊሻገር የሚችለው ዓሳዛኝ በደል የተፈጸመው።’ ዓውሮፓ ህብረት በጨረታው በዓንደኛ ደረጃ ያለፈውን ፕሮቶጀክት ለማሰራት ገንዘብ ከመደበ በሗላ የጨረታው ውጤት ተቀልብሶ ደረጃው ዝቅተኛ የሆነ ብቻ ሳይሆን የቅዱስ ላሊበላን ውድ ህንጻ ከፍተኛ ዓደጋ ላይ የጣለ ፕሮጀክት እንዲሰራ ተወሰነ:: ከዚያም ዓሁን ያለው ዓደገኛ መጠለያ በይድረስ ይድረስ እንዲሰራ ሆነ።

ህዝባችን ውድ መቅደሶቹ እንዲድኑለት በመቸኮሉ ይህ ለምን ሆነ የሚለውን ጥያቄ ዓጥብቆ ዓልጠየቀም። በዚህም ጥፋተኞቹ የዓዳኝነት ትርክት ሰርተው ብቅ ለማለት ቻሉ። ህዝባችን ቶሎ መፍትሄ እንዲገኝ መቸኮሉ ይገባናል። ይህ የኛም ፍላጎት ነው:: ዓሁን ግን ሳናውቀው ሁላችንም ቅርስ ጥበቃ ከሸረበልን ቁጥር ዓንድ ሌብነት ወደ ቁጥር ሁለት ሌብነት እየተዛወርን መሆኑን ባደረግነው ጥናት ዓረጋግጠናል። በላሊበላ ላይ ዓደገኛ መጠለያ ለምን ተሰራ። መልሱ ከሞላ ጎደል ዓሁን ግልጽ ነው። ይህ የተደረገው በቅርስ ጥበቃ አማካኝነት ሁለት የተቀነባበሩ ሌብነቶችን ለመፈጸም ነበር። እነዚህ ሌብነቶች ደሞ የላሊበላ ህንጻን በማውደም የህዝባችንን መንፈሳዊ ጥንካሬና ስነልቦና ለማኮላሸት ያለሙ ነበር። በነሱ ስሌት እነዚህ ሌብነቶች የሚከተሉት ናቸው፣

ሌብነት ቁጥር 1 ለጥገና የተገኘውን ገንዘብ ለመዝረፍ እንዲቻል በዓንደኛ ደረጃ ዓሸንፎ የወጣውን ጨረታ በመቀየር ደረጃው የወረደ መጠለያ ማሰራት። መጠለያው በጊዜዓዊነት የሚሰራው ቋሚ ጥገና ለማካሄድ ነው በሚል እናሳምናለን። ሆኖም እስከመጨረሻው ምንም ዓይነት ጥገና መካሄድ የለበትም። ህንጻው እጅግ መጎዳት ዓለበት። የህንጻው መጎዳት ለኛ የወደፊት ታላቅ የፕሮጀክት ገቢ ምንጭ ይሆናል። ይልቁንም መጠለያው ከመውረዱ በፊት ጥገና ለማካሄድ የሚውለውን በጀት መዝረፍ እንችላለን። መጠለያው ከተሰራ በሗላ እስከሚነሳ ድረስ ለሚከታተሉት ባለሞያወች የተመደበውን ገንዘብም መዝረፍ እንችላለን። ለዩኔስኮ ግን ካስፈለገ መጠለያውን እየተከታተልነው እንደሆነ ዓድርጎ የውሸት ሪፖርት መጻፍ። በሂደት የሚፈጠሩትን የህንጻውን ችግሮች ተጨማሪ ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ፣ ካሜሪካና ከሌሎችም ለማግኛነት መጠቀም። ከውጭ ገንዘብ ከታጣም ከህዝቡ እንዳስፈላጊነቱ ማሰባሰብ።

ሌብነት ቁጥር ሁለት በመጠለያው የደረሰውን ጉዳት ለማከምና ለመንከባከብ በሚል የጥገና ገንዘብ ማፈላለግ መጀመር። 1) መጠለያውን ለማውረድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቅ ዓድርገን ለህዝብ ማቅረብ። መጀመሪያ 20 ሚሊዮን ዶላር እንጠይቅ። ይህ የማይቻል ከሆነ እስከ 10ሚሊዮን ዶላር (300ሚሊዮን) እናደርሰዋለን። ይህ መጠለያውን ለማሰራት ለካምባኒው በኦፊሺያል ከከፈልነው ከ2 እስከ 4 እጥፍ ይበልጣል ማለት ነው። መጠለያው ይነሳ የሚል ጩኸት ሲጀመር ተተኪ የሆነ ፕሮጀክት ማዘጋጀት:: ይህንንም በመጠለያ ካልተሸፈኑት ህንጻወች ላይ ማስጀመር። መጠለያው ሲነሳ ህንጻው ሊሰነጣጠቅ ስለሚችል ስንጥቁን መከላከል የሚችል ሳይንሳዊ እውቀት እንዳገኘን ዓድርገን በመገናኛ ብዙሃን ማስወራት። በዚህ ሂደትም 3 ጥቅም እናገኛለን። መጠለያው የፈጠረውን ችግር ለመቀነስና መጠለያውን ለማውረድ በሚል ከህዝብ፣ ከመንግስትና ከእርዳታ እስከ 20 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ በላሊበላ ላይ በርካታ ዓለማቀፍ የጥገና እርዳታ ዘመቻወች እንዲካሄዱ በማድረግ የማያቋርጥ ስራ መፍጠር ፕሮጀክቶቹ እንደስካሁኑ ጉዳቶቹን የሚያባብሱ እንዲሆኑ ማድረግ። ለዚህም ግድየለሽና በርካሽ የሚሰሩ ድርጅቶችን እንደስካሁኑ ማዘጋጀት። ህንጻው ለዓደጋ ሲጋለጥ በሂደት ከቤተክርስቲያንነት ወደ ታሪካዊ ቅርስነት ብቻ እንዲቀየር የሚያስችል ስምምነት በውጭም በውስጥም በሂደት ማዳበር። ለዚህም የዓካባቢው ህዝብ ከላሊበላ ዙሪያ መነሳቱ ታላቅ ዓስተዋጾ ዓለው።

የላሊበላ ህንጻ ለዓደጋ የተጋለጠው በእድሜው እንደሆነ ዓድርገን በማሳመን የእርዳታ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የዩኔስኮ የተጎዱ ቅርሶች ዝርዝር እንዲገባ ማድረግና በዚያም በኩል የማያቋርጥ ገንዘብ እንዲያመጣ ማስቻል በመጨረሻም የህንጻው ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ፋይዳ እየሟሸሸና እየጠፋ እንዲሄድ በማድረግ የህዝቡን በስልጣኔውና በባህሉ የመኩራትና ከፈረንጆች ጋር ራሱን የማወዳደር ከንቱ ዓባዜ ማክሸፍ:: እኛ ግን እንላለን። ላሊበላን ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ህዝቦችም የማቆየት ታሪካዊ ሃላፊነት ዓለብን።

ላሊበላ ላይ ከዚህ በህዋላ ጅቦች ቦታ ዓይኖራቸውም። የሚከተሉት እንዲደረጉ ዓጥብቀን እናሳስባለን ላሊበላን ለመታደግ ከቅርስ ጥበቃ የበላይ የሆነው የባህል ሚኒስቴር ከቅርስ ጥበቃ መስሪያቤት ባለሞያወችን ብቻ በመጠቀም፣ በላሊበላ ህዝብና በክልልላችን ህዝብ እምነት የሚጣልባቸውን ባለሞያወች በማካተት የስራ እንቅስቃሴውን ይጀምር እንላለን። ህዝባችን የማይደግፋቸውና የማይሳተፍባቸው ውሳኔወች በፍፁም ተግባራዊ ዓይሆኑም በተለይም የቅርስ ጥበቃ ሃላፊወችን በተመለከተ ባለን ተጨባጭ መረጃ መሰረት። የውሸት ሪፖርት ለዩኔስኮ በመጻፉ ላሊበላን በተመለከተ የሚደርሰውን አቤቱታ ሲፈልግ በማስፈራራት ሌላ ጊዜ ደሞ የውሸት ተስፋ በመስጠት ህዝቡን ለከፍተኛ ምሬት በመዳረጉ ቅርሳችንን ያድንልናል የሚል የህዝብ ዓመኔታ ፈጽሞ የሌላቸው በመሆኑ ቀጣይ ሊታሰብበት ይገባል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE