ሱዳን ጥቃት ተፈጽሞ ወታደሮቼ ተገደሉ ስትል ኢትዮጵያ አስተባበለች

ሱዳን በኢትዮጵያ ሠራዊት ጥቃት እንደተፈጸመባትና ወታደሮች እንደተገደሉባት ስታስታውቅ ኢትዮጵያ ግን ክሱን አስተባብላለች። የሱዳን የዜና ወኪል ሱና የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በአልፋሽቃ አካባቢ በተሰማራው የሱዳን ሠራዊት ላይ የኢትዮጵያ ጦርና ሚሊሻ ጥቃት ፈጽመዋል ብሏል።…