በመቀሌ ዛሬ ጧት በድሮን ጥቃት ደረሰ

የኢትዮጵያ መንግስት ጦር የትግራይ ክልል መስተዳድር ርእሰ-ከተማ መቀሌን ዛሬ ጧት በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተነገረ።
የዓይን ምስክሮች እንዳስታወቁት በልማዱ ዲያስፖራ ተብሎ የሚጠራዉ የሐድነት ክፍለ ከተማ የደረሰዉ ጥቃት ሁለት መኖሪያ ቤቶችን አፍርሷል ወይም አቃጥሏል። ነዋሪዎቹ እንዳሉት ሌሎች ቤቶችም መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በሰዎች ላይ ግን ፍርስራሽና የመስተዋት ስብርባሪና ካደረሰዉ አነስተኛ ጉዳት በስተቀር የደረሰ ነገር የለም።
የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቃል አቀባይ ጌታቸዉ ረዳ የዛሬዉን ጥቃት ተስፋ ከቆረጠ ሥርዓት የተሰነዘረ የተስፋ መቁረጥ ርምጃ በማለት ነቅፈዉታል። መቀሌ ባለፈዉ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያም በድሮን ተመትታ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ስለዛሬዉ ጥቃት እስከአሁን ምንም ያለዉ የለም።
ዘገባ ፎቶ፤ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ DW መቀሌ
May be an image of 1 person and outdoors
No photo description available.