ታዋቂ ግለሰቦችና የኢትዮጵያ ቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ሄዱ

May be an image of 10 people, people standing, military uniform and outdoors

 አርቲስት ታማኝ በየነ እና የፖለቲካ ተንታኝና ጸሐፊ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኢትዮጵያ ቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር መሄዳቸው ተሰምቷል።

ፖለቲከኛ ነዓምን ዘለቀ እና ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳም ወደ ግንባር ከዘመቱት መካከል ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የኅልውና ዘመቻ በተለያየ መንገድ ከፊት ሆነው ሲታገሉ የነበሩ አርቲስቶች እና የቀድሞ ሠራዊት የጦር አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ግንባር መዝመትን ተከትሎ እነሱም እንደሚዘምቱ ከዚህ ቀደም ቃል ገብተው ነበር።

በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የኅልውና አደጋ ለመመከት ዛሬ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።