የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚ ዐቢይ የሀገሪቱ ሕገመንግስት በሚፈቅድላቸው መሠረት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ነው – ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ

የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ከፍራንስ 24 ጋር በነበራቸው ቆይታ ካነሷቸው አንኳር ነጥቦች‼️
👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከመንግስታዊ ስራዎቻቸው በተጨማሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው፤ የሀገሪቱ ሕገመንግስት በሚፈቅድላቸው መሠረት ሀላፊነታቸውን እየተወጡም ነው፣
👉 ሕገ-መንግስቱ ከሚፈቅድላቸው ተግባርና ሀላፊነት መካከል የአገሪቱን ጦር በበላይነት መምራት በመሆኑ አሁን አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የያዘውን ዓላማ ለማክሸፍ በጦር ሜዳ ተገኝተዋል፣
👉 መከላከያ ሰራዊቱን መምራታቸው ትክክልና የሚጠበቅ ነው፤ ምክንያቱም አመራርና የጦሩ መሪ እንደመሆናቸው ከፊት ተሰልፈው መምራታቸው ተገቢ ያለው ተግባር ነው፣
👉 አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የሽብር ተግባሩን በአማራና አፋር ክልሎች በማስፋፋት ንጹሐን ዜጎችን ገድሏል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል፣
👉 መንግስት ይህን አረመኔ የሽብር ቡድን መክቶ የዜጎችን ሰላም ከማስጠበቅ ውጭ አማራጭ የለውም፤ መንግስትና ህዝቡ ሳይፈልጉ ተገደው ራሳቸውንና አገራቸውን ለማዳን የገቡበት የሕልውና ዘመቻ ነው፣
👉 በአዲስ አበባ የከተማዋ ነዋሪዎች የተለመደ የእለት ከእለት ተግባሩን በማከናወን ላይ ነው፣
👉 ማህበረሰቡ የአገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት በገንዘብና በቁሳቁስ በመደገፍ አጋርነቱን በከፍተኛ ደረጃ እየገለጸ ይገኛል፣
👉 አሸባሪው ቡድን እንደሚታወቀው ከሕዝቡ የተነጠለ ግፈኛ ቡድን መሆኑ በስልጣን ላይ እያለም ይታወቃል፤ አሁን አየፈጸመ ያለውን ዘግናኝ ግፍ ማህበረሰቡ ከመንግስት ጎን ሆኖ ሀገሩን ለማዳን እየሰሩ ነው፣
👉 ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ የማህበረሰቡን ሰላም የማስጠበቅና የሀገሪቱን ደህንነት የማስጠበቅን ያለመ ነው፣
👉 መንግስት በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው፤ በአሸባሪው ቡድን ተቀባይነት ከማጣታቸውም አልፎ በአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ላይ ግፍና ክህደት ተፈጽመዋል፣