ሽማግሌ ቢጠፋ ዛፍ ገላጋይ ነበር! ወንድሞቼ ነብስሳችሁን ይማርልን! (ሄኖክ አያና)

ያኔ ድሮ አማራ ወጉ ሃያል ነበር! ሊኗኗር ብቻም አደል ሊገዳደል ህግ ነበረው። አማራ ሲገድልም በክብር ነበር፥ መጣሁ ሳይል የወንድ በር ሳይሰጥ ለመግደል አደለም ለማሸነፍም ቃታ አይሰብም!

አማራ እምነትና ደግነት ነበረው! ሊገድለው እድል የመሸበትን ባላንጣውን በዛፍ ቢጠለል ያልፍ ነበር። አማራ ወንድ ነበር፣ መጣሁ ሳይል፣ ታጠቅ ሳይል እጁ አይስትም። ያልታጠቀን አይነካም፥ ብዙ ሆኖ አንድ አይገድልም። ትልቅ ሆኖ ትንሽን፣ ጎበዝ ሆኖ ደካማን ፍጹም አይነካም። አማራ ወጉ ግሩም፣ ልማዱና እሴቱ ድንቅ ነበር። የአማራ ስሪት የሰው ነበር!

ምን ዋጋ አለው ይሄ የኛ የዝቅታ ዘመን ነው። አማራ ቢደኸይም ሃብታም ነበር። በድህነቱ ውስጥ ዘመናትን የተሻገረው በሰውነት ሃብቱ ነው። አሁን ሰውነትም የለ፥ ሃብትም የለ!! መደህየት እሱ ነው። በስማ በለው የበሬ ወለደ ጫጫታ ሙህራን በጠራራ ጠሃይ በማይማን የተወገሩበት ይሄው እኛ ቁልቁል የወረድንበት የኛው ዘመን ነው። ወንድሞቸ ነብስሳችሁን ይማርልን!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE