አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሽብር መንዛቱን ቀጥሏል ።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬን ጨምሮ ሰሞኑን በተከታታይ በሚያወጣቸው መግለጫዎች በሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመፍጠር በሕዝብ ላይ ሽብር መንዛቱን ቀጥሏል። ራሳቸው አሜሪካኖቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት እስካልፈጸሙ ድረስ አዲስ አበባ ሰላም መሆኗን መንግስት በተከታታይ የሚያወጣቸው መረጃዎች የገለጸ ሲሆን አዲስ አበባ መስተዳደር በበኩሉ ዲፕሎማቶችን በመሰብሰብ ገለፃ ማድረጉን የመንግስት ሚዲያዎች ተናግረዋል።

የአሜሪካን ኤምባሲ ዛሬ በለቀቀ መግለጫ እንደገለጸው በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የሽብር ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል አስታውሷል። አሸባሪዎች ዲፕሎማሲያዊ ተቋማትን፣ የቱሪስት ቦታዎችን፣ የመጓጓዣ ማዕከሎችን፣ የገበያ ማዕከሎችን፣ የገበያ ማዕከሎችን፣ የምዕራብ ንግዶችን፣ ሬስቶራንቶችን፣ ሪዞርቶችን፣ የአካባቢ የመንግስት ተቋማትን እና ሌሎች የህዝብ ቦታዎችን በማነጣጠር በትንሽ ወይም ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ሊያጠቁ ይችላሉ። የአሜሪካ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና በባዕድ አገር ዜጎች የሚዘወተሩ ቦታዎችን እንዲያስወግዱ በጥብቅ ይበረታታሉ። ሲል ሊፈፅምና ሊያስፈጽም ያሰበውን የሽብር ጥቃት ገልጻል ።

ይህ የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ በሃገሪቱ ሰላም እንዳሌለ በማስመሰል የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ሰላምን ለማደፍረስ ያቀደው እቅድ እንዳለ አመላካች ነው። ካሁን ቀደም አሜሪካ በተለያዩ ሃገራት እንደምትፈፅመው አይነት የሽብር ድርጊቶችን በመፈጸም የሃገራችንን ሰላም ለማደፍረስ ማሰቧን ያስታውቃል። የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ እንዳሳወቀው የሰላም ጉዳይ ከሕብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት ያረጋገጠው ጉዳይ መሆኑን ገልጿል።

የህወሓት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
በከተሞች በህብረተሰቡ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች በመመሳሰል እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባ እና በዙሪያው ተልእኮ ሰጥቶ በማስገባት ለሽብር ተግባር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እንደተደረሰበት የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።
የሽብር ቡድን አባላቱን በንግድ ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና በሌሎችም የሙያ ስራዎች ህብረተሰቡ ውስጥ ተሰግስገው እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባን እና አካባቢውን ለማተራመስ አቅዶ እየሰሩ መሆኑ ተደርሶበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም ቡድኑ ለሽብር ተልእኮ ያሰማራቸው በርካታ ግለሰቦች በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች ከነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሳሪያ ማለትም ቦንቦች ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘቦችን ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አብራርተዋል።
ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የአፍሪካ የኤዢያና ፓስፊክ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ተደረገ ። በዉይይት መድረኩ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የከተማው የፀጥታ ሀይል ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ እና ከሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።
በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችና ህዝባዊ ሰራዊት የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታን የሚያስከብሩ አደረጃጀቶች እስከ ታችኛው የብሎክ መዋቅር ድረስ በመደራጀት ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሰው፣ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ መሆኗን አንስተዋል ። በምዕራባዊያን ሚዲያዎች የሚነዙትን የፕሮፖጋንዳ እና የሽብር ወሬ መሬት ላይ ካለዉ የከተማዋ የተረጋጋ ሰላም ጋር ፍፁም የሚጋጭ በመሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ቀነዓ ያደታ ገልጸውላቸዋል ።