የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጋር መከሩ።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በአማራ ክልል እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አስመልክቶ ለአምባሳደሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሽብር ቡድኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
May be an image of 2 people and people sitting