ምዕመናንና ሀገርን መጠበቅ ሰላምን መሻት የቅድስት ቤተክርስቲያን ግብርና ተልዕኮ ነው – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

በየዓመቱ ጥቅምት 12 የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።

በሰላም እጦትና አለመረጋጋት ሳቢያ በንፁሃንና በሀገር ደህንነት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ህዝበ ምዕመኑ ፀሎትና ተማፅኖውን እንዲያበረታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቅርባለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ምልዓተ ጉባዔን አስጀምረዋል።

ምዕመናንና ሀገርን መጠበቅ ሰላምን መሻት የቅድስት ቤተክርስቲያን ግብርና ተልዕኮ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ለወገን ሰላም የሃይማኖት አባቶችና አብያተ ክርስቲያናት ተግተው እንዲፀልዩ አሳስበዋል።

ሰላም ለመንፈሳዊም ለዓለማዊ እንቅስቃሴ እጅጉን አስፈላጊ ነው ያሉት ፓትሪያርኩ በተወሰኑ አካባቢዎች ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ምዕመኑ ፀሎትና ልመናውን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።