የኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ የመፍረስና የውድቀት መነሻ ተፈልጎም ይሁን ሳይፈለግ መንገዱ ወደ አከራካሪ የጥላቻ ንግግሮች ለማምራቱ አንዱ መንስኤ ነው

DW ፡ ለ30 ዓመታት ያህል በተጓዘው የኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ ላይ ሁለት አንኳር ሃሳቦች ይነሳሉ።አንደኛው ወገን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ውቅር ሂደት ብቻ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን ሲያወሳ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን የመፍረስና የውድቀት መነሻ አድርገው የሚያቀርቡ አሉ።ብሄርን መሰረት አድርጎ የዘለቀው የአገሪቱ ፖለቲካ ያመጣቸው ትሩፋቶች እንዳሉ በመሞገት በአግባቡ ሊያዝ ይገባል የሚሉም ከመሃል አልታጡም፡፡ግን ደግሞ አብዛኛዎቹ በአንድ ሃሳብ ይስማማሉ፤ተፈልጎም ይሁን ሳይፈለግ መንገዱ ወደ አከራካሪ የጥላቻ ንግግሮች ለማምራቱ አንዱ መንስኤ መሆኑን። የጀርመን ድምፅ ራዲዮ በጉዳዩ ላይ ባለሞያ አነጋግሯል።