በእስክንድር ነጋ ላይ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጽሞበታል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስክንድር ነጋ ጋር ጦርነት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስክንድር ነጋ ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። በእስክንድር ነጋ ላይ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጽሞበታል ። እስክንድር እስር ቤት ውስጥ መደብደቡንና ጉልበቱ መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ የተባሉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል!
በዚህም ምክንያት ጉልበቱ መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ የተባሉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል! በዛሬው ዕለት እስክንድር ነጋ ችሎት መቅረብ አልቻለም ።ይህም በመሆኑ በተከታታይ ምስክር የመስማት ቀጠሮ ተሰርዞ ፤ ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ተዘዋውሯል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ችሎት ለመታደም የተገኙ በጅምላ ታፍሰው ልደታ ፖሊስ ጣቢያ መመሪያ ተወስደዋል ።
May be an image of one or more people

በልደታ ፍርድ ቤት የእነ እስክንድርን ችሎት ተከታትለው ሲወጡ የነበሩ በፖሊስ ታፍሰው ወደ ልደታ ፖሊስ መምሪያ ተወስደዋል!!

በትላንትናው ምሽት በእስክንድር ላይ የግሩፕ ጥቃት ተፈጽሟል ። የጥቃቱ ድርጊቱን ተከትሎ የከፋ ጉዳት በእስክንድር ላይ አለመድረሱን ስንታየሁ ቸኮል ለእኔ እና ለነብዩ ውብሸት ገልጾልናል ። ይህ መረጃ ይፋ እስከ ሆነበት ድረስ እስክንድር ማንንም ለማናገር ፍቃደኛ ባለመሆኑ ለማግኘት አልተቻለም ። እስክንድር ሰዎችን ለማገኝት ያለ-መፈለጉ ምክንያት በተመለከተ ስንታየሁ እንደነገረኝ ከሆነ ” በተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ያዘነ እና የተበሳጨ በመሆኑ ፤ በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኖ ማንንም ለማግኘት አለመፈለጉን ” ነግሮናል።

የእኔ ጥርጣሬ ግን ፤ እስክንድርን በአካል አግኝቼው እንዳላናግረው የፈለገው ለምን ይሆን ?! ተናግሮኝ አይዋሸኝምና በአካሉ ላይ የሚታይ ነገር ካለ እኔም ለምን እለዋለው ?! እናም ለምን ይሆን እስኬ ሰውን ማግኘት ያልፈለገው ?! ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስንታየሁ ሰኞ በፍርድ ቤት ለዳኞች እና ለችሎት ታዳሚ እንዲሁም ለህዝብ የምንገልጸው ነገር ፤ አለ ብሎኛል ። ሁሌም ቢሆን በአካል እና በመንፈስ ከእኛ ጋር ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ ብሏል ። ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት !
ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ታዳሚው ጥሎ ከወጣ በኋላ በቀጠለው ችሎት የተናገረው፦
አቶ እስክንድር ከተያዙበት ሰኔ 24 ጀምሮ አብሬያቸው አለሁ። ገና ሲያዙ ተደብድበዋል። ቃሊቲ ተደብድበዋል። በተደጋጋሚ ነው እየተደበደቡ ያሉት። ሌላም እስክንድር ላይ የሚፈፀም ስንታየሁ ላይ የማይፈፀም፤ ስንታየሁ ላይ የሚፈፀም እስክንድር ላይ የማይፈፀም አለ። ዛሬ እስክንድር ላይ ስለተፈፀመው ድብደባ ችሎቱ መነጋገር ያለበት እስክንድር በተሰየበት ነው። “ስንታየሁም እስክንድር ባለበት ነው ዝርዝሩን የምንናገረው” ብሏል። ፍርድ ቤቱ ይሄን ሃሳብ ይቀበልና ለሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን። እኛ ጠበቆችም ቂሊንጦ ሄደን እናግኘው።